ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በነዛው የሀሰት ወሬ ተደናግረው የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቹ እየተመለሱ ነው
—-
ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በነዛው የሀሰት ወሬ ተደናግሮ ቤት ንብረታቸው ጥለው የሸሹ የአማራ ክልል ተወላጆች ወደቤታቸው እየተመለሱ ነው፡፡ ተመላሾች የትግራይ ሠራዊት በየመንገዱ እያደረገላቸው ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የፋሽስቱ ቡድን የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲል ህዝባዊ አላማን አንግቦ ፍትሓዊ ጦርነት እያካሄደ ላለው የትግራይ ሠራዊት ሌላ ስም በመስጠት ህዝቡ ተረጋግቶ እንዳይኖር እያደረገ ነው፡፡ ፋሽሽቱ በነዛው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የወልድያ፣ ሀራገበያ፣ መርሳና ውጫሌ ነዋሪዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ወደ ደሴና ኮምቦልቻ እንዲሸሹ ከማድረጉ በተጨማሪ በእድሜ የገፉ እናቶችን በመኪና ይዞ ሄዶ ደሴ ላይ ጥሏቸዋል፡፡
የትግራይ ሠራዊት በገባባቸው ቦታዎች ሰላምና መረጋጋት በመፈጠሩ ምክንያት ሸሽተው የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ወደቀያቸው እየተመለሱ ነው፡፡
ህፃናትን እና በእድሜ የገፉ እናቶችን በየገደሉና በየሸንተረሩ በእግራቸውን አቆራርጠው እየተመለሱ ሲሆን የትግራይ ሠራዊት ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ፋሽስቱ በማይታመንም ላሱ አሁንም የውሸት ወሬ እየነዛበ መሆኑ ህዝቡ በውሸት ፕሮፖጋንዳው ሳይታለል የሸሸውን ወደ ቤቱ እንዲመለስ ያልሸሸውን ደግሞ ተረጋግቶ በቤቱ እንዲቀመጥ መክረዋል፡፡
በይብራህ እምባየ


