

ጀግናው የትግራይ ሠራዊት ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋር በመተባበር በፋሽስት ቡድን በከሚሴ ከተማ ታስረው የነበሩ 55 የትግራይ ተወላጆች ነፃ አወጣ፡፡
-*************************************
እስረኞች በእስር ቆይታቸው ከፍተኛ ግፍና ስቃይ እንደደረሰባቸውም ተናግረዋል፡፡
በአውደ ውግያ ከፍተኛ ሽንፈት እየተከናነበ ያለው የፋሽስቱ ቡድን የትግራይ ተወላጆችን ማሰርና ማሳደድ የእለት ተእለት ስራው አድርጎታል፡፡
ፋሽስቱ በደሴ እና አካባቢው ለበርካታ አመታት ይኖሩ የነበሩ 55 የትግራይ ተወላጆች ትግራዋይ በመሆናቸው ብቻ ከሶስት ወራት በላይ አስሯቸዋል፡፡
ጀግናው የትግራይ ሠራዊት ደሴን ሲቆጣጠር ቁስለኛውንና ሬሳውን ማንሳት ያልቻለው የፋሽስቱ ሠራዊት የትግራይ ተወላጆችን በጅምላ ለመግደል ወደ ከሚሴ ከተማ ይዛቸው ፈረጠጠ፡፡
የትግራይ ሠራዊት ከኦሮሞ ነፃናት ሠራዊት ጋር በመሆን ሞታቸውን ሲጠባበቁ የነቡሩት የትግራይ ተወላጆች ጥበብ በተሞላበት መንገድ እስረኞቹን ካለ ምንም ጉዳት ማስፈታት ችለዋል፡፡
በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ አቶ መሓሪ ወልደገብርኤል፣ አቶ ግደይ ገብረዝጌአብሄር እና በመንገድ ስራ ፕሮጀክት ተሰማርቶ የነበሩት አቶ ዮናስ ተስፋይ ከታሳሪዎች መካከል ሲሆኑ የፋሽስቱ ሠራዊት ለህወሓት በገንዘብ ትደግፋላችው በማለት ንብረታቸው ዘርፎ በርካታ ግፍና ስቃይ እንዳደረሰባቸው ነው የሚገልጹት፡፡
በፋሽስቱ ቡድን ልንረሸን ቀናችን እየተጠባበቅን በነበርንበት ጊዜ የትግራይ ሠራዊት እና የኦሮሞ ነፃናት ሠራዊት ጥረት በህይወት እንድንተርፍ አድርጎናል ብለዋል፡፡
በይብራህ እምባየ