ከትግራይ መንግስት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

ከትግራይ መንግስት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

በደም የተነከረ የፋሽሽት ኣብይ ኣህመድ ቡድን ዕድሜ ለማራዘም ሲባል፣ ህፃናትን የእሳት እራት በማድረግ ላይ ያለው ኣረመኔው ቡድን ይብቃህ በማለት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ድምፁ ሊያሰማ ይገባል!


በሕገ-ወጥ መንገድና በማጭበርበር የስልጣን ጥመኛ ፋሽሽት ቡድን፤ ካለፉት ሶስት ኣመታት ተኩል ጀምሮ እስከ ዛሬ ጥቅምት 12/2014 ዓ.ም የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ፤ከምድረ ገፅ ለማጥፋት፡ ዕድሜ፣ፆታ፣ሃይማኖት፣የስራ ሁኔታ ወዘተ ሳይለይ በኣየር እና በምድር ህዝብን የማጥፋት ጅምላዊ የጀኖሳይድ ጭፍጨፋ ኣካሂደዋል፡፡ ኣሁንም በማካሄድ ላይ ነው፡፡

ኣረመኔው የፋሽሽት ኣብይ ኣህመድ ቡድን በኣጠቃላይ ባለፉት 11 ወራት በተለይም ካለፈው ሰኔ ወር 2013 ዓ.ም እስከ ኣሁን ድረስ ባሉት ኣራት ወራት በትግራይ ሰራዊት ኣይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ሽንፈት በተጎነጨባቸው ሁሉም ዓውደ ውግያዎች የፋሽሽት ሰራዊቱ በትግራይ፣ አማራና፣ ኣፋር በረሃዎች፣ ሜዳዎች፣ ተራራዎች፣ ኮረብታዎች እና ሸለቆዎች እንደቅጠል ረግፈዋል፡፡ የሀገሪቱ ማህበረ ኢኮኖሚ ምስቅልቅሉ ኣውጥቶ በውጭ ምንዛሬ የገዛቸው ዘመናዊ የጦር መሳርያዎችም የትግራይ ሰራዊት ንብረት ሆነዋል፡፡

ነገር ግን ፋሽሽት ቡዱኑ ይህንን ሁሉ ሽንፈት ተከናንቦም ቢሆን ለህዝብና ለሀገር ህልውና ቅንጣት ታክል እንደማይቆረቆርና ደንታ ቢስ መሆኑን በተግባር በማሳየት ላይ ነው፡፡ ይኸውም በማደናገር በዋነኛነት በኣስገዳጅ ኣፍሶ በየጦር ግንባሩ እየማገዳቸው ያሉት ለኣቅመ ሄዋንና ኣዳም ያልደረሱ ህፃናት እንዲሁም ዕድሜያቸው የገፋ ኣዛውንቶች ሳይወዱ በግድ የእሳት እራት እየሆኑ መሆናቸው በትግራይ ህዝባዊ ሰራዊት የተማረኩ ዕድሜያቸው 14፣15፣16 የሆኑ ህፃናት እንዲሁም ምንም ዓይነት የጦር መሳርያ ተኩሶው የማያውቁ ሽማግሌዎች ህያው ምስክር ናቸው፡፡ ይህንን በዓለም ኣቀፍ ፍርድ ቤት በጦር ወንጀለኝነት የሚያስከስስ ድርጊት እውነት መሆኑን ማረጋገጥ ለሚፈልግ ማንኛውም ንፁህ ህሊና ያለዉ ሰው፣ ዓለማቀፍ ማህበረሰብ፣ የሰብኣዊ መብት ተማጓች እና የግብረ ሰናይ ተቋም በኣጠቃላይ እያንዳንዱ ባለድርሻ ኣካል የትግራይ መንግስት በሩን ክፍት ኣድርጎ ሃቁን ለማሳየት ዝግጁ እና ፍቃደኛ መሆኑን በዚህ ኣጋጣሚ ሊገልፅ ይወዳል፡፡

የፋሽሽት ኣብይ ኣህመድ ቡድን በኣጠቃላይ ባለፉት 11 ወራት በተለይም ከመስከረም 27/2014 ዓ.ም ጀምሮ በኣራት ግንባሮች በትግራይ ሰራዊት ላይ በከፈተው ጦርነት የሞቱ፣ የቆሰሉ እና የተማረኩ የኣረመኔው ቡድን ቅጥረኛ ታጣቂዎች የሚበዙት ህፃናትና ወጣቶች መሆናቸው በእጅጉ ያሳዝናል፡፡ በነዚህ ግንባሮች በነበረው ፍልምያ የታየው ሌላ ኣስደንጋጭ ጉዳይ ኣንድ ጠመንጃ ለኣራትና ለኣምስት ሰዎች ኣንዳንዴም ምንም ዓይነት ጦርነት የማያውቁ ኣርሶ ኣደሮች ባዶ እጃቸውን ወደ ጦርነቱ ኣስገብቶ የኣሞራ ሲሳይ እያደረገቸው ይገኛል፡፡

ይህ ኣረመኔ ቡድን በጭፍራ፣በውጫሌ እና በወገል ጤና ግንባሮች ወዘተ የደረሰበት ሽንፈት ለመሸፋፈን የዘወትር የቅጥፈት ተግባሩ የሆነውን የበሬ ወለደ ውሸት የታከለበት የመግለጫ ጋጋታ ነጋ ጠባ በመለፈፍና የክተት ነጋሪት በመጎሰም እንዲሁም መቐለ ከተማ በጦር ኣውሮፕላኖች በተከታታይ ቀናት በመደብደብ የንፁሃን ደም በማፍሰስ ውርደቱንና ሽንፈቱን ለማካካስ በመፍጨርጨር ላይ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ የዚህ ውጤት የፋሽስቱ ቡድን እድሜ ለማሳጠር የትግራይን ህዝብ ለበለጠ ትግል ተጠናክሮ እንዲዘምት የሚያደርግ ነው።

ሰሞኑም ይህ ፋሽሽት ቡድን ሌላ ተጨማሪ ደም ሊያፈስ፤ “ደቡብ ወሎና ኣማራን ታደጉ” ወዘተ የሚል ሌላ የጥፋት ጥሪ በማስተጋባት ላይ ይገኛል፡፡ ነገር ግን በኣሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ በፊት ከትግራይ ሰራዊት ጋር ተዋግተው በመቶ ሺዎች የተደመሰሱ ልጆቻችን የት ገቡ ብሎ የፋሽሽት ቡድኑን ሊጠይቅ ይገባል፡፡ “እስከ መቼስ ነው ኣንዳችም ጥቅም ለማናገኝበት ጦርነት ልጆቻችን የምንገብረው” ብሎ ሊነሳ ይገባል፡፡ ባጭሩ በደም የተነከረንና የሰላም ጥሪን ወደ ጎን ኣሽቀንጥሮ ኢትዮጵያ ደም እንድታነባ ያደረገው እና በማድረግ ላይ ያለውን የፋሽሽት ኣብይ ኣህመደ ቡድን ዕድሜ ለማራዘም ሲባል ህጻናትን የአሳት እራት በማድረግ ላይ ያለው አረመኔ ቡድን ይብቃህ በማለት እያንዳንዱ የኢትዮጵያዊ ድምፁ የሚያሰማበት ወቅት ኣሁን መሆኑን ኣውቆ የድርሻው ሊወጣ ይገባል፡፡

የህፃናት ደም በከንቱ መፍሰስ ሊቆም ይገባል!
የትግራይ መንግስት

ጥቅምት 12/2014 ዓ.ም
መቐለ

Published by Woyanay Tigray Media

This Websites for the support of the people of Tigray and for the various ideas on the human and democratic rights of all Ethiopian nationalities.the equality of the Ethiopian people has always been a victory for the TPLF and the people of Tigray. Therefore, we will only distribute the TPLF’s contribution to the country to our people. We will discuss various realities of the people of Tigray as well as the heroism of Tigray and the positive issues we need to support for our government in Tigray. The heroism of the TPLF, the TPLF is a real and heroic party built by political elites who will not betray the country and sell it to the enemy.

One thought on “ከትግራይ መንግስት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

Comments are closed.

%d bloggers like this: