ጠላቶች እንዳይመረጥ የቻሉትን ሁሉ ቢሞኩሩም፦ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ግንበድጋሚ የአለም ጤና ድርጅትን እንዲመራ ተመርጠዋል። ለ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ቤተሰቦችና ትግራዊያን እንዲሁም አፍሪካውያን እንኳን ደስ አላችሁ!

ዶር ቴድሮስ አድሐኖም ለሁለተኛ ግዜ የአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር መሆኑ ተረጋጠ!!
*********************************
የቀድሞው የውጭ ጉዳይ እና የጤና ሚኒስትር የነበረው ዶር ቴድሮስ አድሐኖም ለአለም የጤና ድርጅት [the World Health Organization (WHO)] ዳይሬክተርነት እንዲሾም ሐገሩ ኢትዮጵያ ድጋፍ ብትነፍገውም በድጋሜ ለአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ሆኖ እንደሚመረጥ ተረጋገጠ፡፡ ኢትዮጵያ ድጋፍ የነፈገችው ትግራዋይ በመሆኑ እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግስት፤ በኤርትራ እና በUAE የተፈጸመውን የትግራይን ወረራ በአደባባይ በመቃወሙ ብቻ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዶክተሩ ላይ በኢትዮጵያ መንግስት የተፈጸመው ይህንን የዘር ተኮር ጥላቻ የአለም ሐገሮች ስላወቁት የኢትዮጵያ ድጋፍ ለዶክተሩ መከልከሉ ማንም ቦታ አልሰጠውም፡፡ በተጻራሪው የኢትዮጵያ የጥላቻ አካሄድ ሌሎች ለፍትህ የማይደራደሩ የሰለጠኑ ሐገሮች በተለይ እንደ ጀርመን ያሉ ከዶክተሩ ውጪ ማንም መሆን እንደሌለበት በመመስከር መከታ ሊሆኑለት ችለዋል፡፡

ባጠቃላይ ዶር ቴድሮስ ባለው ከፍተኛ የአፈጻጸም ብቃት እና ችሎታ የተነሳ በድርጅቱ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣ መሪ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ የተነሳ ኬንያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሐገሮች የደገፉት ሲሆን፤ ሁሉም ምዕራባውያን እና ቻይናን ጨምሮ ወሳኝ ሐገሮች በሙሉ ለሁለተኛ ግዜ ድርጅቱን እንዲመራ በሙሉ ድምጽ ድጋፋቸውን ለግሰውታል፡፡ ኢትዮጵያ ሴጣንም ቢሆን ይሾም እንጂ ዶክተር ቴድሮስ እንዳይቀጥል ብትፍጨረጨርም አፍራ ከመመለስ ውጪ ያገኘችው ነገር የለም፡፡ የኢትዮጵያ የቅናት እና የጥላቻ አካሄድ አንድም ሐገር ከዶክተሩ ጋር እንዳይወዳደር በር በመክፈቱ የተነሳ ብቻውን ተወዳድሮ ያለ ማንም ተቀናቃኝ ስራውን ለሁለተኛ ግዜ ለ5 አመት የሚቀጥል ይሆናል፡፡

መልካም የስራ እና የስኬት ዘመን ለዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እንዲሆን እመኛለሁ፡፡ ይህ ኢትዮጵያ ያፈራችው ዶክተር የአለምን አንዱን ቁልፍ ስራ በዚህ ብቸኛ ሰው የሚኖርባት ምድር ላይ ሲዘውር ከማየት በላይ የሚያኮራ ነገር የለም፡፡ የዶክተሩ ብቃት ከኢትዮጵያ ተርፎ ለአፍሪካ ኩራት ቢሆንም ምቀኛ አጥፍጦ ጠፊ ከመሆን አይቦዝንም፡፡ አፍሪካኖች ዶክተሩ ጥቁር በመሆኑ ብቻ የኩራ ምንጫቸው ስለሆነ ሲደግፉት፤ ኢትዮጵያ ግን ትግራዋይ በመሆኑ እንዳይመረጥ ያልፈነቀለችው ድንጋይ የለም፡፡ ይህ ክስተት አስገራሚ ነው፤ ትግራይ ልገንጠል ብለው ቢናገሩ ተገቢ መሆኑ ይህ ኩነት እንድ ምስክር ነው፡፡ በእኔ እይታ ዶክተሩ በጣም የተረጋጋ እና አስተዋይ የሆነ ሁሉን የሚወድ እና ግፍን እና በደልን አምርሮ የሚጠላ ጀግና ሰው ነው፡፡ ስኬቱ አስደስቶኛል!!

‘’ጠላት አያሳጣኝ‘’ ማለት እንደዚህ አትራፊ ስለሚያደረግ ነው!!

Published by Woyanay Tigray Media

This Websites for the support of the people of Tigray and for the various ideas on the human and democratic rights of all Ethiopian nationalities.the equality of the Ethiopian people has always been a victory for the TPLF and the people of Tigray. Therefore, we will only distribute the TPLF’s contribution to the country to our people. We will discuss various realities of the people of Tigray as well as the heroism of Tigray and the positive issues we need to support for our government in Tigray. The heroism of the TPLF, the TPLF is a real and heroic party built by political elites who will not betray the country and sell it to the enemy.

%d bloggers like this: